የጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ
የማኀበሩ የተፈረመ ዋና ገንዘብ (ካፒታል)፡- ብር 21,290,000.00
የማኀበሩ ዋና ገንዘብ (የተከፈለ ካፒታል)፡- ብር 11,205,000.00
የምዝገባ ቁጥር፡- BL/AA/3/0054856/2017
የማኀበሩ ዋና መሥሪያ ቤት፡- አዲስ አበባ ከተማ፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 4፣ የቤት ቁጥር 111/4/5
ሲድ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ቅዳሜ ህዳር 6 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ ቅ/ዑራኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ የተቋሙ ዋና መ/ቤት ደጎል ህንፃ 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘዉ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ያካሄዳል፡፡
የ2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች
- የጉባኤውን አጀንዳ ማፅደቅ
- የተሸጡ አክሲዮኖችንና የአክሲዮን ዝውውሮችን ማጽደቅ
- እ.ኤ.አ እስከ ጁን 30 ቀን 2025 ድረስ ያለውን የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርትን ማድመጥና ማጽደቅ፤
- እ.ኤ.አ እስከ ጁን 30 ቀን 2025 ድረስ ያለውን የዉጭ ኦዲተሮች ሪፖርትን ማድመጥና ማጽደቅ፤
ስለሆነም ማንኛውም ባለአክሲዮን ወይም ህጋዊ ተወካይ ከላይ በተጠቀሰው ዕለት በቦታው ተገኝተው እንዲሳተፉ ማኀበሩ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን በጉባኤው ላይ መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች በንግድ ህጉ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 አንቀጽ 377 መሠረት ጉባኤው ሊካሄድ ሶስት ቀናት እስኪቀረው ድረስ አዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው በማኀበሩ ዋና መ/ቤት ቦሌ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 4፣ የቤት ቁጥር 111/4/5 ደጎል ህንፃ 4ኛ ፎቅ ላይ ቀርበው የውክልና ፎርም እንዲሞሉና ተወካይ እንዲሰይሙ እናሳስባለን፡፡ በተጨማሪም ሁሉም ባለአክሲዮኖች ማንነታቸውን የሚገልጽ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፍቃድ ይዘው እንዲቀርቡ በአክብሮት ይጠይቃል፡፡
የዳይሬክተሮች ቦርድ
