ጠቅላላ ጉባኤ
የማኀበሩ የተፈረመ ዋና ገንዘብ (ካፒታል)፡- ብር 21,290,000.00
የማኀበሩ ዋና ገንዘብ (የተከፈለ ካፒታል)፡- ብር 10,655,000.00
የምዝገባ ቁጥር፡- BL/AA/3/0054856/2017
የማኀበሩ ዋና መሥሪያ ቤት፡- አዲስ አበባ ከተማ፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 4፣ የቤት ቁጥር 111
ሲድ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ 1ኛ መደበኛ እና 1ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤውን ቅዳሜ መጋቢት 27 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ ቅ/ዑራኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ የተቋሙ ዋና መ/ቤት ደጎል ህንፃ 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘዉ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ያካሄዳል፡፡
የ1ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች
- የጉባኤውን አጀንዳ ማፅደቅ
- የተሸጡ አክሲዮኖችንና የአክሲዮን ዝውውሮችን ማፅደቅ
- ለዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት የሥራ ዋጋ ላይ ተወያይቶ መወሰን
- ከ2017-2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ኦዲት የሚያደርግ የውጪ ኦዲተር መምረጥና ማፅደቅ
- በተጓደለዉ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ምትክ ምርጫ ማካሄድና ማጽደቅ
- የጉባኤውን ቃለ ጉባኤ ማዳመጥና ማጽደቅ
የ1ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች
- የጉባኤውን አጀንዳ ማፅደቅ
- የማኀበሩን መመስረቻ ጽሁፍ ማሻሻልና ማጽደቅ
- የማኀበሩን ዋና ገንዘብ ማሳደግ
- የጉባኤውን ቃለ ጉባኤ ማጽደቅ
ስለሆነም ማንኛውም ባለአክሲዮን ወይም ህጋዊ ተወካይ ከላይ በተጠቀሰው ዕለት በቦታው ተገኝተው እንዲሳተፉ ማኀበሩ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን በጉባኤው ላይ መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች በንግድ ህጉ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 አንቀጽ 377 መሠረት ጉባኤው ሊካሄድ 3 ቀናት እስኪቀረው ድረስ አዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው በማኀበሩ ዋና መ/ቤት ቦሌ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 4፣ የቤት ቁጥር 111 ደጎል ህንፃ 4ኛ ፎቅ ላይ ቀርበው የውክልና ፎርም እንዲሞሉና ተወካይ እንዲሰይሙ እናሳስባለን፡፡ በተጨማሪም ሁሉም ባለአክሲዮኖች ማንነታቸውን የሚገልጽ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፍቃድ ይዘው እንዲቀርቡ በአክብሮት ይጠይቃል፡፡
የዳይሬክተሮች ቦርድ