ሲድ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ
ለሲድ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ
ባለአክሲዮኖች በሙሉ
ጉዳዩ-የአክሲዮን ሽያጭን ይመለከታል፤
ተቋማችን ሲድ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ በመጋቢት 27 ቀን 2017 ዓ.ም በ1ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ መሰረት፣ ቀደም ብለው የተፈረሙት 21,290 አክሲዮኖች እያንዳንዳቸው 1,000 ብር ያላቸው ሙሉ ለሙሉ ተከፍለው ሲያልቁ፣ ተጨማሪ 60,000 አክሲዮኖች ለሁሉም ባለአክሲዮኖች እንዲደለደል መወሰኑ ይታወሳል፡፡
በዚሁ መሰረት ቀደም ሲል የተፈረሙት አክሲዮኖች ተከፍለው መጠናቀቃቸውን በማሳወቅ ለሁሉም ባለአክሲዮኖች 60,000 አክሲዮኖች የተደለደሉ ሲሆን፤ ከዚህም ውስጥ ተጨማሪውን 23,106 (ሃያ ሶስት ሺ አንድ መቶ ስድስት) አክሲዮኖችን ለመግዛት ፍላጎታቸውን ያሳወቁ ሲሆን ቀሪው 36,894 (ሰላሳ ስድስት ሺ ስምንት መቶ ዘጠና አራት) አክሲዮኖችን ግን ነባር ባለአክሲዮኖች ለመግዛት ፍላጎት እንደሌላቸው ቦርዱ ተገንዝቧል፡፡
ስለዚህም በአሁኑ ወቅት የተደለደለላቸውን አክሲዮኖች ለመግዛት ፍላጎት በሌላቸው ብዛታቸው 36,894 (ሰላሳ ስድስት ሺ ስምንት መቶ ዘጠና አራት) አክሲዮኖች እያንዳንዳቸው ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) የሆኑ በድምሩ ብር 36,894,000.00 (ሰላሳ ስድስት ሚሊዮን ስምንት መቶ ዘጠና አራት ሺ ብር) አክሲዮኖችን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል መግዛት የምትፈልጉ ነባር ባለአክሲዮኖች በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ማለትም እስከ ነሐሴ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ብቻ ባለአክሲዮኖች ፍላጎታችሁን እንድታሳውቁን በትህትና እየጠየቅን ከተጠቀሰው ቀነ ገደብ ውጪ ቀሪዎቹን አክሲዮኖች ለአዲስ ባለአክሲዮኖች የሚዘዋወር መሆኑን ቦርድ ያሳውቃል፡፡ እንዲሁም ቀደም ሲል ተጨማሪውን አክሲዮኖች ለመግዛት ፍላጎት አሳይታችሁ ሙሉውን ክፍያ ያላጠናቀቃችሁ ባለአክሲዮኖች በተቻለ ፍጥነት ሙሉውን ክፍያ በቶሎ እንድታጠናቅቁ የዳይሬክተሮች ቦርድ በትህትና ይጠይቃል፡፡
ከሠላምታ ጋር
የዳይሬክተሮች ቦርድ
Contact as
Head Office +251115316231
Urael Branch +251115316052
seedmicrofinanceinstitution@gmail.com