ሲድ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ
የአክሲዮን ድልድልን ይመለከታል፤
የሲድ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ በመጋቢት 27 ቀን 2017 ዓ.ም በ1ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ መሰረት፣ ቀደም ብለው የተፈረሙት 21,290 አክሲዮኖች እያንዳንዳቸው 1,000 ብር ዋጋ ያላቸው ሙሉ ለሙሉ ተከፍለው ሲያልቁ፣ ተጨማሪ 60,000 አክሲዮኖች ለሁሉም ባለአክሲዮኖች እንዲደለደል መወሰኑ ይታወሳል፡፡
በዚሁ መሰረት ቀደም ሲል የተፈረሙት አክሲዮኖች ተከፍለው ስለተጠናቀቁ ተጨማሪ 60,000 አክሲዮኖች ለሁሉም ባለአክሲዮኖች ተደልድሏል፡፡ ይህ መደልደያ በአንድ ዓመት ውስጥ ተከፍሎ መጠናቀቅ አለበት፣ እንዲሁም አንድ አራተኛ ወይም ሩቡን በመጀመሪያው ክፍያነት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ማለትም እስከ ታህሳስ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ካልተከፈለ የተደለደለው አክሲዮን ሙሉ በሙሉ ለሌሎች ባለአክሲዮኖች ወይም ለሌሎች ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ይዘዋወራል።
ስለዚህም ከታህሳስ 06 ቀን 2018 ዓ.ም በፊት ቅ/ዑራኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ በሚገኘው የተቋሙ ዋና መ/ቤት ደጎል ህንፃ 4ኛ ፎቅ ላይ በመምጣት የተደለደለላችሁን የአክሲዮን መደልደያ ቅጽ እንድትወስዱና በጊዜ ግዴታችሁን እንድትወጡ የዳይሬክተሮች ቦርድ ያሳውቃል፡፡
ሲድ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ